Test Page
Click here for a list of include paths
ጽህፈት ቤት ለመፍጠር የየየሁኔታው ርዕሰ ጉዳይ መልእክት በመስጠት የአምራች ባለሥልጣናትን በፍጥነት ወደየትኛውም የሶፍትዌር ተፅእኖ መንገዶች በፍጥነት ለመድረስ ይዳረጋሉ
በሞባይል ስልካችን ውስጥ ስላሉት ወሳኝ ማዕድናት ምን ያውቃሉ?
- የቢቢሲ ቪዥዋል እና ዳታ ጆርናሊዝም ቡድን
- ዓለም
ዓለም የአየር ንብረት ለውጥን እያስከተለ ያለውን ነዳጅ ዘይት መጠቀምን እንዴት ሊያቆም ይችላል?
መልሱ ኪስዎ ውስጥ ነው።
በስልኮቻችን ውስጥ ያሚገኙት ወሳኝ ማዕድናት ለቤት ውስጥ እና ለትራንስፖርት የሚያገለግል ከነፋስ እና ከፀሐይ የሚገኝ ንጹህ ኃይልን የሚያመነጩ ባትሪዎች ለማምረት በጣም አስፈላጊ ናቸው።
በስልክዎ ውስጥ ያትኞቹ ማዕድናት እንደሚገኙ ለማወቅ ወደ ታች በማንሸራተት ይመልከቱ።
የሞባይል ስክሪን፣ ማይክሮ ቺፕስ፣ ገመዶች እና ባትሪውን ጨምሮ በውስጡ ያሉትን ክፍሎች ለማሳየት የቀረበ የሞባይል ምስል።
የሞባይልዎን የውስጥ ክፍል ከፍተው በያዩ ይህንን ይመለከታሉ።
ሞባይልዎ ኃይል እንዲያገኝ በውስጡ የተለያዩ ማዕድናት ይገኛሉ። ባትሪው ውስጥ ኒኬል፣ ሊቲየም እና ኮባልት የተባሉ ማዕድናት አሉ።
እነዚህ ማዕድናት ከሞባይል በተጨማሪ ለቤታችን፣ ለቢሯችን እና ለመኪኖቻችን የሚያስፈልገውን ኃይል በማቅረብ በአውሮፓውያኑ 2030 ብክልትን ወደ ዜሮ ለማውረድ ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል።
በስልኩ ውስጥ ያሉ አያያዥ ገመዶች፣ ሰርኪዩትቦርድ፣ ባትሪ እና ሽፋኑ።
ኒኬል በተጨማሪም በሌላም የስልካችን ክፍል ውስጥም ይገኛል። እንዲሁም ማዕድኑ የሕክምና መሳሪያዎችን ጨምሮ በተለያዩ ምርቶች ውስጥ ይገኛል።
የስልክ ባትሪ
ሊቲየም ማዕድን በአእምሮ ሕክምና ውስጥ 'ለስሜት ማረጋጊያ' መድኃኒትነት በባለሙያዎች ይታዘዛል።
የስልክ ባትሪ
ኮባልት በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለው ቻርጅ ለሚደረጉ ባትሪዎች ነው። በተጨማሪም ጌጣጌጦች ውስጥ ይገኛል።
ለምን በባትሪዎች ላይ አተኮርን? ምክንያቱም እነዚህ ሦስት ማዕድናት የአየር ንበረት ለውጥን ለመግታት ጥረት ለሚያደርጉ አገራት ወሳኝ በመሆናቸው ነው።
ለኤሌክትሪክ መኪና የሚያገለግለው ባትሪ ወሳኝ የሚባሉትን ማዕድናት በመጠቀም ቀዳሚው ነው።
የዓለም ኃይል ተቋም እንዳለው በ2020 (እአአ) በዓለም ዙሪያ ከተሸጡ 25 አዳዲስ መኪኖች መካከል አንዱ የኤሌክትሪክ ነበር። በዚህ ዓመት ከአምስት አንድ ይሆናል ተብሏል።
አረንጓዴ ከሚባሉ የኃይል ምንጮች ቻርጅ የሚደረጉት የኤሌክትሪክ መኪኖች፣ ነዳጅ ከሚጠቀሙት ከአራት እና ከዚያም በላይ በሆነ እጥፍ ብክለትን ይቀንሳሉ።
አረንጓዴ ቴክኖሎጂ የሚባሉት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ፣ የኤሌክትሪክ መኪኖች እና የነፋስ ኃይል ማመንጫዎች በሙሉ ወሳኝ የሚባሉት ማዕድናት ያስፈልጓቸዋል።
በሚቀጥሉት 20 ዓመታት የኤሌክትሪክ መኪኖች እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማከማቻ ቁሶች ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። በዚህም ምክንያት የእነዚህ ወሳኝ ማዕድናት ፍላጎትም ከፍ ይላል።
ለወሳኝ ማዕድናቱ ያለውን ፍላጎት እንመልከት።
ብክለትን ወደ ዜሮ ለማውረድ ሲታቀድ የማዕድናቱ ፍላጎት እንዴት ይጨምራል? (ዜሮ ብክለት የሚባለው ወደ ከባቢ አየር በካይ ጋዝ እንዳይጨመር ማድረግ ነው።)
ይህ ማዕድን ማውጫ የሚያስፈልገንን የማዕድን መጠንን የሚወክል ነው (መጠኑን በትክክል የሚያሳይ አይደለም)።
ይህ ባለፈው ዓመት ምን ያህል የኒኬል ማዕድን በዓለም ዙሪያ ጥቅም ላይ እንደዋለ ያሳያል: 3,200 ኪሎቶን (የ3.2 ሚሊዮን መኪኖች ክብደትን ያህል ይሆናል)።
በ2030 (እአአ) ዜሮ ብክለት ላይ ለመድረስ፣ 5,700 ኪሎቶን የሚገት የኒኬል ማዕድን ያስፈልገናል።
ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ያለው የኒኬል የአቅርቦት መጠን 4,140 ኪሎቶን ሲሆን፣ ይህም በ2030 ሊደረስበት ከታሰበው የዜሮ ብክለት ፍላጎት ዝቅ ያለ ነው።
ሊቲየም እና ኮባልትን ደግሞ እንመልከት።
ሊቲየም: ፍላጎት በ2022, 146 ኪቶ; ዜሮ ብክለት በ2030, 702 ኪቶ; በ2030 የሚፈለገው አቅርቦት, 420 ኪቶ.
የዓለም ሙቀትን በ1.5 ሴሊሺየስ ለመገደብ በ2030 (እአአ) የሊቲየም አቅርቦትን መጨመር ያስፈልጋል።
ኮባልት: ፍላጎት በ2022, 200 ኪቶ; በ2030 ዜሮ ብክለት, 346 ኪቶ; በ2030 የሚፈለገው አቅርቦት, 314 ኪቶ.
የዓለም ሙቀትን በ1.5 ሴሊሺየስ ለመገደብ በ2030 (እአአ) የኮባልት አቅርቦትን መጨመር አለብን።
እነዚህ ማዕድናት በዓለም ዙሪያ ከየትኞቹ አገራት እንደሚወጡ እንመልከት።
በ2022 ኢንዶኔዢያ፣ ፊሊፒንስ እና ሩሲያ ከዓለም የኒኬል ማዕድን አቅርቦት ውስጥ ሁለት ሦስተኛውን አምርተዋል።
አውስትራሊያ፣ ቺሊ እና ቻይና ለዓለም ከቀረበው የሊቲያም ማዕድን ውስጥ 91 በመቶውን አምርተዋል።
ዲሞክራቲክ ኮንጎ, አውስትራሊያ እና ኢንዶኔዢያ የዓለምን 82% የኮባልት ማዕድን አቅርቦትን አውጥተዋል።
ዲሞክራቲክ ኮንጎ, ኮባልት: 74%; ኢንዶኔዢያ, ኒኬል 49%; አውስትራሊያ, ሊቲየም 47%
በጣም ተፈላጊ የሆኑትን ማዕድናት የማውጣት ተግባር በከፍተኛ ደረጃ በተወሰኑ አገራት ውስጥ የሚከናወን ነው። እያንዳንዱን ማዕድናት የሚያመርቱ ቀዳሚ አገራት የሚከተሉት ናቸው።
እነዚህ ማዕድናት የት ነው የሚመረቱት?
ማዕድናቱ የሚወጡባቸው ስፍራ እና የሚመረቱባቸው ስፍራዎች ከመልክዓ ምድር አኳያ በተወሰኑ አካባቢዎች የሚከናወን ነው።
ቻይና, ኮባልት 74%, ሊቲየም 65%; ኢንዶኔዢያ, ኒኬል 43%.
ቻይና ከፍተኛ መጠን ያለው ሊቲየም እና ኮባልት የሚመረትባት ስትሆን፣ ኢንዶኔዢያ ደግሞ አብዛኛውን ኒኬል ታመርታለች።
ቻይና, ኮባልት 74%, ሊቲየም 65%, ኒኬል 17%.
ቻይና ለዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የሚያገለግሉ 90% ልዩ ማዕድናት ታመርታለች።
በታሪክ እንደታየው ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በተገቢው ሁኔታ ለማግኘት የንግድ እና የአቅራቢዎችን ብዛት ማስፋት ካልተቻለ ከባድ አደጋን ይከተላል።
ቲም ጉልድ. አይኢኤ
የማዕድን ማውጫ ማሽን ቺሊ ውስጥ በሚገኝ የሊቲየም ማዕድን ማውጫ የጨው ተረፈ ምርትን ሲዝቅ
የሊቲየም ማዕድን ማውጫ በቺሊ
እነዚህን አስፈላጊ ማዕድናትን ለማቅረብ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች ምንድን ናቸው?
አንድ የማዕድን ማውጫ በአግባቡ ሥራውን ለማከናወን 15 ወይም ከዚያ በላይ ዓመታትን ይፈልጋል። ከተቀመጠው ብክለትን ዜሮ የማድረስ ግብ ላይ ለመድረስ የቀሩት ሰባት ዓመታት ብቻ ናቸው።
ዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ በሚገኝ የኮባልት ማዕድን ማውጫ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ የምትሰራ ሴት
የኮባልት ማዕድን ማውጫ በዲሞክራቲክ ኮንጎ
አንድ የማዕድን ክምችት ከተገኘ በኋላ ማዕድኑን አውጥቶ ለመጠቀም መንገድን የመሳሰሉ መሠረተ ልማቶች በአካባቢው ላይኖሩ ይችላሉ።
አዲስ የማዕድን ማውጫዎች ደኅንነታቸው የተጠበቀ ላይሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመግባባት ተገቢ እና ፍትሃዊ የድርሻ ክፍፍል እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል።
በዲሞክራቲክ ኮንጎ የኮባልት እና ኮፐር ማዕድናትን ማውጣት በከፍተኛ ሁኔታ ሲስፋፋ፣ የአካባቢውን ማኅበረሰብን ማፈናቀል እና ከባድ የመብት ጥሰቶች እንዲፈጸሙ ምክንያት ሆኗል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል
ጊዜ እየተለወጠ ሲሄድ ባትሪዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል።
አብዛኞቹ የኤሌክትሪክ መኪኖች ባትሪዎች ከ20 ዓመት በኋላ መለወጥ እንዳለባቸው ሳይንቲስቶች ያምናሉ።
በዩኬ ቢርሚንግሃም ዩኒቨርስቲ የሚገኙ አጥኚዎች እንደሚሉት በባትሪ ውስጥ ካሉ ግብአቶች ውስጥ ከግማሽ ያነሱት መልሰው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
በሚቀጥሉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ግን 80% የባትሪ ክፍሎች መልሰው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
ባትሪዎች መልሰው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማስቻል ባትሪዎቹ የሚሰሩበትን መንገድ ማጤን ያስፈልጋል።
ፕሮፌሰር ፖል አንደርሰን ከዩናይትድ ኪንግደም ቢርሚንግሃም ዩኒቨርስቲ
አሁን እየተመረቱ ካሉት ባትሪዎች አኳያ፣ ከእነዚህ መካከል መልሶ በመጠቀም የምንፈልገውን ማግኘት አንችልም። የሚያስፈልጉንን ባትሪዎች ለማምረት የሚበቃ ማዕድን አስካሁን ገና ተቆፍሮ አልወጣም።
ፕሮፌሰር ፖል አንደርሰን ከዩናይትድ ኪንግደም ቢርሚንግሃም ዩኒቨርስቲ
ተሳታፊዎች
ዝግጅት እና አርትኦት፡ ኬት ፎርብስ፣ አንድሩ ዌብ፣ አሌክሳንድራ ፋውቺ፣ ሊዮኒ ሮበርትሰን፣ አና ሉሺያ ጎንዛሌዝ
ዲዛይን፡ ማሪያም ኒካን፣ ራኢስ ሁሴይን፣ ማት ቶማስ እና ሳሊም ኩራሺ
የተዘጋጀው: በማቲው ቴይለር፣ በአሊሰን ሹልስ
ሙከራ፡ አዳም አለን የፕሮጀክት ኃላፊ: ሆሊ ፍራምፕተን
ምሥሎች: ጌቲ ኢሜጅስ
ምንጮች: የዓለም ኃይል ተቋም፣ አይሪና ዩናይትድ ኔሽንስ ኤልዛቤት ፕሬስ፣ ፕሮፌሰር ፒ. አንደርሰን እና ዶ/ር ጂ. ሃርፐር፣ ቢርሚንግሃም ሴንተር ፎር ስትራተጂክ ኤለመንትስ ኤንድ ክሪቲካል ማቴሪያልስ፣ የቢርሚንግሃም ዩኒቨርስቲ፣ ዩናይትድ ኪንግደም
የሕይወት ወዳጃዊ መረጃ ፣ የእነሱ አመለካከት ፣ የውይይት ፣ የአደረጃጀት ፣ የገበያ ፣ ወዘተ ፣ ዋና ኢላማ ግቦች ተመሳሳይ ናቸው ፡፡ የግ The መመሪያ ቁርጠኝነት ተገልጻል ፡፡ አሁን የእንግሊዝኛ ነፃነት አርዕስት በክፍል አልተገለጸም ፡፡ ጃን ዲሻም የዓለም የሃርድዌር አስፈላጊው የጠንቋዮች የማማከር ቡድን ግን
እና 450 የአካል ብቃት መመሪያ ግcha የርዕሰ ጉዳይ ርዕሰ ጉዳዮች ኢኮኖሚያዊ መዋቅሮች የቋንቋ መሣሪያዎች የእኛ እገዛ የሕንድ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ትክክለኛ ችሎታ አላቸው ፈቃድ መስጠት ያለ ትንተና ግዥ ይመስላል ፡፡ ኡሽኪ የአሁኑን የማንነት መመሪያ አስተርጓሚ አተረጓጎም አሚኪክumar Sunat የሰዎችን ትምህርት መምረጥ የሚችል ይመስላል
መሰረዝ በቃ ሊከናወን ነው ፣ ነገር ግን የተጠቃሚው መረጃ ሊቀርብ ይችላል። ግን የተቋቋመው የተሟላ ውይይት መሰባበር አይቻልም ፣ ግን መመሪያዎቹ ሊሻሻሉ ይችላሉ። የመጀመሪያው ዓለምን እንደ ህብረተሰብ ማቆየት ነው ቋንቋ የኅብረተሰቡ ቋንቋ ነው