ከአውሮፓውያኑ 1952 ጀምሮ በአህጉረ አፍሪካ 130 የሚሆኑ የተሳኩ የመንግሥት ግልበጣዎች ተካሂደዋል። የግብፁ ንጉሥ ፋሩክ የመጀመሪያው በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱ የሀገር መሪ ናቸው።
በአፍሪካ ባለፉት 3 ዓመታት ስምንት የተሳኩ የመንግሥት ግልበጣዎች ተካሂደዋል። አዲሱ የመፈንቅለ መንግሥት ማዕበል ወታደራዊ ግልበጣዎች እስከ 2020 ድረስ ቀዝቀዝ ብለው ድጋሚ ያንሰራራበት ወቅት ነው። በርካታ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በአህጉሪቱ ውስጥ ያጋጠመው በ1970ዎቹ ነበር።
በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጡ አንዳንድ መሪዎች ለበርካታ አስርት ዓመታት በመንበራቸው ላይ ቆይተዋል። ሌሎች ደግሞ ሥልጣን በያዙ በቀናት ውስጥ ተፈንግለዋል።
ለምሳሌ የኢኳቶሪያል ጊኒው ፕሬዝደንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ በ1979 ሥልጣን ከያዙ በኋላ ለ44 ዓመታት መንበራቸው ላይ ቆይተዋል።
በዚህም በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ለበርካታ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩ መሪ ለመሆን ችለዋል።
ለምሳሌ የኢኳቶሪያል ጊኒው ፕሬዝደንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ በ1979 ሥልጣን ከያዙ በኋላ ለ44 ዓመታት መንበራቸው ላይ ቆይተዋል።
በዚህም በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ለበርካታ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩ መሪ ለመሆን ችለዋል።
በሳህል ቀጣና የሚገኙ በርካታ ሀገራት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥታት ተካሂደውባቸዋል። የመፈንቅለ መንግሥት ቀጣና በተባለው አካባቢ በቅርቡ የተካሄዱት መፈንቅለ መንግሥታት በኒጀር እና በጋቦን ውስጥ ያጋጠሙ ናቸው ነው።
በ2020 እና 2021 በማሊ ወታደራዊ መፈንቅለ-መንግሥታት ተደርገዋል። በ2021 በቻድ,በጊኒ እና በሱዳንም መፈንቅለ መንግሥታት ተካሂደዋል። ቡርኪና ፋሶ በ2022 ሁለት የመንግሥት ግልበጣዎችን አስተናግዳለች። ከሱዳን በስተቀር ሁሉም ሀገራት የቀድሞ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ነበሩ።
ከ2000 (እአአ) በኋላ ከተካሄዱ 26 የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥታት 19ኙ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በነበሩ ሀገራት ውስጥ የተፈፀሙ ናቸው። ይህ አሀዝ በአፍሪካ የፈረንሳይ ተፅዕኖ አሉታዊ ውጤት አለው የሚል ሃሳብ በአንዳንዶች ዘንድ እንዲነሳ አድርጓል።
የመፈንቅለ መንግሥት ብዛት
0
2
4
6
8
በርካታ የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት በተደጋጋሚ የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥታት ተካሂደውባቸዋል። ቢያንስ አራት መፈንቅለ መንግሥታት ካጋጠሟቸው 17 የአፍሪካ ሀገራት ግማሹ የሚገኙት በምዕራቡ የአህጉሪቱ ክፍል ነው።
ቡርኪና ፋሶ በርካታ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደባት የአፍሪካ ሀገር ስትሆን,ስምንት ጊዜ መፈንቅለ መንግሥት ተከስቶባታል። ሲራ ሊዮን እና ኡጋንዳ እያንዳንዳቸው 7 ጊዜ መፈንቅለ-መንግሥት በማካሄድ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ከአፍሪካ ሀገራት አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት እና በተለይ በደቡባዊ እና ምሥራቅ ክፍል የሚገኙ ሀገራት ናቸው የተሰካ መፈንቅለ መንግሥት ያልገጠማቸው።
በ2024፤ 34 ዓመት የሆናቸው ኢብራሒም ትራኦሬ በዓለም በዕድሜ ትንሹ የሀገር መሪ ናቸው። መስከረም 30/2022 የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የቡርኪና ፋሶ ጊዜያዊ መሪ ሆነዋል። ከዚያ ቀደም ጊዜያዊ ፕሬዝደንት የነበሩት ፓል-ሄንሪ ሳንዳዎጎ ዳሚባ ከመንበራቸው ተፈንቅለዋል።
90 በመቶው የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥታት የተካሄዱት በወታደራዊ ኃይል ታግዘው ሲሆን,4 በመቶው ደግሞ በቅጥረኛ ወታደሮች አመካይነት የተፈፀሙ ናቸው። ሌሎች የመፈንቅ-መንግሥት ዓይነቶች ሰላማዊ ተቃውሞ,ቅኝ ገዢ ኃይሎች,በአማፂያን እና በቤተ-መንግሥት ውስጥ የተካሄዱ ናቸው።
አብዛኞቹ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዙ መሪዎች በጉልበት ከሥልጣን እንዲወርዱ ተደርገዋል፤ አሊያም ተገድለዋል።
በ1972 ጄኔራል ኢግናቲየስ ኩቱ አቼያምፖንግ፤ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን የጋናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ኮፊ ቡሲያን ደም ባላፈሰሰ መንገድ ከሥልጣን ፈነገሉ። ከስድስት ዓመታት በኋላ ቤተ-መንግሥት ውስጥ በተካሄደ የመንግሥት ግልበጣ በተወገዱ በአንድ ዓመቱ በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ተፈርዶባቸዋል።
ቶማስ ሳንካራ የቁም እስር ላይ ሳሉ ነው በእሳቸው ስም በ1983 የቡርኪና ፋሶ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደው። ሳንካራ፤ ጥቅምት 15/1987 በብሌይዝ ኮምፓዎሬ በተመራ ታጣቂ ቡድን ተገድለዋል።
ጃፋር ኒሜይሪ የሱዳኑን መሪ የነበሩትን ኢስማኢል አል-አዣሪን አስወግደው ሥልጣን የያዙት በ1969 ነበር። መጀመሪያ የወታደራዊው ቡድን መሪ ሆነው,ቀጥሎ ደግሞ ፕሬዝደንት ሆነው ካገለገሉ በኋላ በ1985 ከመንበራቸው ተፈንግለዋል።
ዦን-ባፕቲስት ባጋዛ የቡሩንዲውን ፕሬዝደንት ሚኬል ሚኮምቤሮን በ1976 ከሥልጣን አስወግደው ሥልጣን ከያዙ ከአስራ አንድ ዓመታት በኋላ ከመንበራቸው ተነስተው ለስደት ተዳርገዋል።
ኦማር አል-በሽር ወደ ሥልጣን የመጡት በ1989 ነበር። በወቅቱ የሱዳን ጦር ብርጋዴር ጄኔራል ነበሩ። ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መርተው በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን አስተዳደር ጥለው ሥልጣን ያዙ። እስከ 2019 ድረስ በተለያዩ ማዕረጎች ሱዳንን ሲያስተዳድሩ ከቆዩ በኋላ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተባረሩ።
ፍራንሷ ቦዚዜ ያንጎቮንዳ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ስድስተኛው ፕሬዝደንት የሆኑት በ2003 ወደ ሥልጣን ከመጡ ከ10 ዓመታት በኋላ ከሥልጣናቸው ተወገዱ።
የቤተሰብ ጉዳይ
በአንዳንድ ሀገራት ሥልጣን ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ነው። የኢኳቶሪያል ጊኒው ፕሬዝደንት ፍራንሷ ማሲያስ ንጉዌማ ደም አፋሳሽ በሆነ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት በዘመዳቸው ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ ነው። በ2024 ቴዎዶሮ በዓለማችን ከሚገኙ ንጉሣዊ ያልሆኑ እና ለረጅም ዘመን በሥልጣን ላይ የቆዩ ሁለተኛው መሪ ናቸው።
ሎረንት ካቢላ በ1997 ሞቡቱ ሴሴ ሴኮን ፈንቅለው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሦስተኛው ፕሬዝደንት ሆኑ። ሎረንት ካቢላ ከጠባቂያቸው በአንዱ ሲገደሉ የ29 ዓመቱ ልጃቸው ጆሴፍ ካቢላ ተኳቸው።
ጥናት፡ ሩት ሙላንዲ፤ ጽሁፍ እና የመረጃ ትንተና፡ ዶሮቲ ኦቲየኖ፤ ዲዛይን፡ ሚሊሰንት ዋቺራ፤ ዝግጅት፡ ዴቪድ አዩላ እና ቦአዝ ኢቼንግ፤ አርትኦት፡ ዳሚሎላ ኦጂቱንዴ እና ዶሮቲ ኦቲየኖ። ተጨማሪ ድጋፍ፡ ኦላኒዬ አዴቢምፔ,ጆርጅ ዋፉላ,ማዮዋ አላቢ,ብራያን ኦቲየኖ,አሽሊ ላይም እና ኤስተር ኦጎላ።
ጌቲ ኢሜጅስ እና የአፍሪካ መንግሥታት ድረ-ገፆች