የማራቶን ሩጫ ውድድር ከኦሊምፒክ ጋር በእጅጉ ይዛመዳል፤ ዘመናዊው የኦሊምፒክ ውድድር ከተጀመረበት እንደ አውሮፓውያኑ ከ1896 ጀምሮ ማራቶን የውድድሩ አካል ነው።
የማራቶንን 42.2 ኪሎ ሜትሮች በፍጥነት መሮጥ ከፍ ያለ ጽናትን ከሚጠይቁ ውድድሮች መካከል አንዱ የሚያደርገው ሲሆን፤ ውድድሩ ሯጮችን ከፍተኛ መጠን ያለው ኃይል እንዲያቃጥሉ ያደርጋል።
ታዲያ እነዚህ ሯጮች ምን ያህል ኃይል ነው የሚያቃጥሉት? በዚህ የረቀቀ የስፖርት ሳይንስና የተመጣጠነ ምግብ ባለበት ዘመን ውስጥ እነዚህ የማራቶን ባለክብረ ወሰን ሯጮች ምን አይነት ምግብ ነው የሚመገቡት?
አስኪ በአሁኑ ወቅት በወንዶችና በሴቶች የማራቶን ውድድር የዓለምን ክብረ ወሰንን የያዙት ኬንያውያን ሯጮች ኢሉድ ኪፕቾጌ እና ብሪጂድ ኮስጌይ የሚመገቡትን እንመልከት።
ሁለቱ ሯጮች ለቶኪዮው ኦሊምፒክ ዝግጅት ልምምድ ሲያደርጉ አግኝተን ስለአመጋገብ ልምዳቸው ለማወቅ ጥረት አድርገናል።
በዚህ ታሪክ ውስጥ ወደ ደታች በመውረድ በደማቁ የተጻፉትን ቃላት በመጫን የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን ባሌቶቹ ብሪጂድ እና ኢሉድ የሚመገቧቸውን ኃይል ሰጪ ምግቦችና መጠጦችን ይመልከቱ።
ማራቶን ከፍተኛ ላብ የሚፈስበት ውድድር ሲሆን ይህንን ለመተካት ሯጮቹ ምን እንደሚጠጡ በመመልከት እንጀምር። የሯጮቹ አገር ኬንያ በመሆኗ ሻይ ቀዳሚ ምርጫቸው ነው። በስኳር የሚጠጡት ሻይ ፈጥነው ወደ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።
ጣፋጭ በበርካታ ኬንያውያን ሯጮች ዘንድ ተወዳጅ ነው። አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከምግባቸው ውስጥ አንድ አምስተኛውን የካርቦሃይድሬት ይዘት የሚሸፍነው ስኳር ነው። .
በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ አንዳንድ ሯጮች በልምምድ ወቅት ከውሃ ይልቅ በርከት ያለ ሻይ ይጠጣሉ። ከውድድር በፊት አምስት ብርጭቆ ሻይ ከጠጡ ከ450 ካሎሪ ጋር የሚመጣጠን ኃይል ያገኛሉ።
አስራ አምስት ማንኪያ ስኳር በጣም ብዙ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ገና ብዙ ይቀራል።
አሁን ለሯጮቹ ምግብ የሚቀርብበት ጊዜ ነው።
ጥሩ የሚባለው የመጀመሪያው የምግብ ምርጫ ፣ ኬንያ ውስጥ ተወዳጁ ምግብ ሲሆን ከበቆሎ የሚሰራ ገንፎ ነው።
ኡጋሊ ብዙም የማያስወጣ ምግብ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ኡጋሊ ለኬንያውያን የረጅም ርቀት ሯጮች የሚያስፈልገውን ኃይል በመስጠት ወሳኝ ነው። ይህም በአጠቃላይ ከሚያስፈልጋቸው ጉልበት ውስጥ አንድ አራተኛውን ይሸፍናል።
በቶኪዮው ኦሊምፒክ ላይ ግን ሌላ አማራጭ ምግብ ይመገባሉ። ብሪጂድ እንዳለችው "ኬንያ ውስጥ እንዳለው በሌሎች አገራት ውስጥ ኡጋሊ የለም። ምናልባት ሩዝ፣ ፓስታ ወይም ዶሮና ዓሳ ልንመገብ እንችላልን።"
ነገር ግን ሯጮቹ በሚመርጧቸው የምግብ አይነቶች ላይ እናተኩር፤ ስለዚህም አንድ ጊዜ የተበላው ብቻውን በቂ ስላልሆነ ሌላ ሁለተኛ እንጨምር።
ኡጋሊ ጥሩ ምግብ ነው፣ ነገር ግን ሯጮቹ የሚያስፈልጋቸውን የኃይል መጠን ለማግኘት ብዙ ይቀራቸዋል።
በእርግጥም ገንፎ ብቻውን በቂ አይደለም፤ እስኪ ከምግባቸው ዝርዝር ውስጥ ምን ምን ሌሎች ነገሮች እንደተካተቱ እንመልከት።
የበሬ ሥጋ በትክክል ጠቃሚ ነው፤ ነገር ግን ወደ ሌሎች የምግብ አይነቶች እንለፍ።
የበሬ ሥጋ የፕሮቲን ጥሩ ምንጭ ሊሆን ይችላል፤ በርካታ ኬንያውያን ሯጮች ግን የሚያስፈልጋቸውን ፕሮቲን ከወተትና ከባቄላ ያገኛሉ። ስለዚህ ከሁለቱ የተወሰነ እንቀላቅል።
ወተት ኬንያውያን የሚሉት መጠጥ ዋነኛ ግብአት ነው። ይህ በዝንጅብልና በቅመም የተዘጋጀ የኬንያውያን ጣፋጭ ሻይ ሲሆን ሯጮቹ ሁለት ብርጭቆ ይጠጣሉ። ይህም 320 ካሎሪ ይሆናል ማለት ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ኢሉድ ሌላ የሚመርጠው የሚጠጣ ነገር አለ "ሙርሲካ! ይህ የወተት አይነት ለስፖርተኛ በጣም ጠቃሚ ነው። ስትጠጡት ምግብ የማዋሃድ አቅማችሁን ያፋጥነዋል" ይላል።
ከኡጋሊ ጋር ተቀቅሎ አንድ ጊዜ የሚቀርበው የባቄላ አይነት ሰውነታችን የሚያገኘውን የኃይል መጠን በ120 ካሎሪ ከፍ ያደርገዋል። አሁንም የሚቀር የምግብ አይነት አለ፤ እሱም ድንች ነው።
ታዋቂ ኬንያውያን ሯጮች በርካት ያለ ሩዝ፣ ድንች እና ዳቦ ይመገባሉ። ይህ ደግሞ በግምት በጣም የሚያስፈልጋቸውን የካሎሪ መጠን አንድ አራተኛውን እንዲሁም አንድ ሦስተኛውን የካርቦሃይድሬት መጠን ይሰጣቸዋል። በዚህም ለማራቶን ውድድራቸው የሚያስፈልጋቸውን ጉልበት ያሰባስባሉ።
ሁለት ጊዜ ገበታቸው ላይ በቀረበ ሩዝና አንድ ጊዜ በሚቀርበው የተቀቀለ ስኳር ድንች ምን ያህል ኃይል እንደሚያገኙ እንመልከት።
ታዲያ ይሄ በሴቶች የማራቶን ሩጫ ሻምፒዮን ለሆነችው ብሪጂድ ውድድሯን ለማጠናቀቅ የሚበቃ ኃይል ይሰጣታል? አዎ!
ብሪጂድ በ2019 (እአአ) የቺካጎ ማራቶንን ስታሸንፍ 1,666 ያህል ካሎሪ ተጠቅማለች።
ይህንን በአጭሩ ለማስረዳት ብሪጂድ በሮጠችበት 2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ውስጥ ብቻ አንዲት አማካይ አዋቂ ሴት በቀን ውስጥ መመገብ ያለባትን የኃይል መጠን አቃጥላለች።
አሁን ደግሞ ወደ ኢሉድ ኪፕቾጌ እንመለስ። ኪፕቾጌ ከብሪጂድ በክብደትም ሆነ በፍጥነት ስለሚበልጥ የማራቶን ውድድሩን በድል ለመጨረስ ከእሷ በለጥ ያለ ኃይል ያስፈልገዋል።
ለዚህ ደግሞ ከተጠቀሱት ምግቦች በተጨማሪ የተጠበሰ እንቁላል፣ ጎመንና ሌሎች ቅጠላ ቅጠሎችን ጨምሮ ይመገባል።
በዚህም ኢሉድ ኪፕቾጌ ከሁለት እንቁላሎችና ከተለያዩ ቅጠላ ቅጠሎች 260 ተጨማሪ ካሎሪ ያገኛል።
እነዚህ ምግቦች ከዚያው ከኬንያ የሚገኙ ሲሆኑ፤ ቆስጣን የሚመስለው ከተለያዩ ቅመማ ቅመሞች ጋር ተዋህዶ የሚቀርብ ነው።
በምሥራቅ አፍሪካ አገራት በስፋት የሚገኘውና የጎመን ዝርያ የሆነው የተባለው ቅጠልም ከምግቡ ውስጥ ይካተታል።
"አትክልቶችን ከገበያ አዳራሾች አንገዛም። በአብዛኛው ጎመንና ቆስጣን እራሳችን ነን የምናበቅላቸው። መሬታችን ለም ስለሆነ ኬሚካል አንጠቀምም" ስትል ብሪጂድ ለቢቢሲ ተናግራለች።
አሁን ወደ ማጠናቀቂያው እየደረስን ነው። ይህም ቀለል ያሉ ነገሮች የሚቀርቡበት ነው።
እንደሁሉም ሰው ታዋቂ ሯጮች ቀለል ያለ ምግብን ይመርጣሉ። ከሁሉም በጣም የሚመርጡት ደግሞ ፍራፍሬዎችን ነው።
"በተለይ እኔ የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎችን በጣም እወዳለሁ" ትላለች ብሪጂድ። "ዛሬ ምናልባት ሙዝ ልበላ እችላለሁ፣ ነገ ደግሞ ብርቱካን፣ በቀጣይ ደግሞ ማንጎ ይሆናል።"
ለየት ያለ ለስላሳ መጠጥም በጣም እንደምትወድ ተናግራለች።
ለአሁን ግን ጤናማ በሆኑት ነገሮች ላይ እናተኩር፤ ሙዝ 100 ካሎሪ ይዟል።
ኢሉድ በ2018 አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ባስመዘገበበት ጊዜ በአጠቃላይ 2,322 ካሎሪ አቃጥሏል።
በዚህም አንድ አዋቂ ወንድ በቀን ውስጥ ማግኘት ይገባዋል የሚባለውን 2,500 ካሎሪ፣ ኪፕቾጌ በ2 ሰዓት ከ1 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ውስጥ ጥቅም ላይ አውሏል።
በመመልከት በምን ያህል ካርቦሃይድሬትና ካሎሪ የተሞላ መሆኑን ይረዱ።
ሁለቱም ኢሉድ ኪፕቾጌ እና በሪጂድ ኮስጌይ በዚህ ዓመት በሚካሄደው በታላቁ የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ።
ከምሥራቅ አፍሪካ የወጡ ሯጮች በኦሊምፒክ ላይ የሚካሄደውን የማራቶን ወድድር በበላይነት ይዘውታል። የአካላቸው አወቃቀርና በስምጥ ሸለቆ ከፍታማ ቦታዎች ላይ የሚያደርጉት ልምምድ ከሚመገቡት ምግቦች ጋር በውድድሩ ላይ ለሚያገኙት ስኬት የእራሳቸው የሆነ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይታመናል።
ኢሉድ ለቢቢሲ እንደተናገረው ጥሩና የተመጣጠነ ምግብ ወሳኝ ነገር ነው "ለሩጫ ጉልበት ስለሚያስፈልግ የምንመገበው ነገር በጣም ወሳኝ ነው።"
የዓለማችን ዋነኛ የስፖርት ውድድሮች በዘመናዊ መልክ ለተለያዩ ተግባራት በተዘጋጁ ገንቢ የምግብ ምርቶች ላይ መሠረታቸውን ያደረጉት ቢሆንም፤ አንዳንድ ኮከብ ስፖርተኞች ግን አሁንም ያልተወሳሰቡ፣ ቀላል ተፈጥሯዊ ምግቦችን እንደሚመገቡ መዘንጋት የለበትም።

ሯጮቹን በውድድር ጊዜ ጉልበት ለማመንጨት በሚያስፈልጋቸው ተቀራራቢ የኃይል መጠን ስሌት ላይ ደርሰናል። በዚህ ስሌት ዝቅተኛው የኃይል መጠን 1 ሲሆን ይህም አንድ ሰው ሲቀመጥ የሚያወጣው ኃይል ነው። የማራቶን ሩጫን የመሳሰሉ ሌሎች ከበድ ያሉ እንቅስቃሴዎች ደግሞ 19.8 ኃይልን ይፈልጋሉ።
ስለዚህም አንድ ሯጭ ምን ያህል ኃይል እንደሚያቃጥል ለማወቅ ከላይ የተጠቀሰው የኃይል አጠቃቀም በሯጩ ክብደት እንዲሁም ሩጫው በሚቆይበት የሰዓት መጠን ማስላት ያስፈልጋል።
ስለዚህ የኢሉድ ኪፕቾጌ የዓለምን ክብረ ወሰን የያዘበትን ሰዓት ማራቶን ለመሮጥ የሚያስፈልገውን የኃይል ስሌት መጠን በ19.8 እንዲሁም በክብደቱ 58 ኪሊ ግራም እና ሩጫውን ጀምሮ ባጠናቀቀበት 2.02 ሰዓት በማብዛት ለማወቅ ይቻላል።
ስለዚህም 19.8 X 58 X 2.02 = 2,320 ካሎሪ ይሆናል። .
በምግቦቹና በመጠጦቹ ውስጥ ያለውን የካሎሪ መጠን ለማስላት ከሁለት ዓመት በፊት የወጣውን የኬንያ ምግብ ይዘቶች ዝርዝር እዚህ ላይ ለማጣቀሻነት ጥቅም ላይ ውሏል። በዚህም ከእያንዳንዱ ምግብና መጠጥ የሚገኘው የካሎሪ መጠን ወደ ተቀራራቢው 10 ካሎሪ እንዲጠጋ ተደርጓል።
አዘጋጆች፡ ቱራል አህመድዛዲ፣ ሊዮኒ ሮበርትሰን፣ ዮሃንስ ዴል እና ሮቤርቶ ቤሎ ሮቬላ። የመስክ ጥንቅር፡ ሙቶኒ ሙቺሪ፣ ግሎሪያ አቼንግ እና ንጆሮጌ ሙይጋይ። ንድፍ፡ በሾን ዊልሞት፣ ኦላኒ አዴቢምፔ እና ማሪያም ኒካን። የቴክኒክ ቅንብር፡ ማርከስ ጉርጌል፣ ሺልፓ ሳራፍ እና ሳሊ ሞራሌስ። ምስጋና፡ ለዶ/ር ጀስቲን ሮበርትስ፣ አንግሊያ ሩስኪን ዩኒቨርስቲ የጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አመጋገብ ተባባሪ ፕሮፌሰር።